ሞኙ ሰውና ብልህ ባሇቤቱ
ተረት ተረት
በአንዴ ወቅት አንዴ ሞኝ ሰው ከሌሎች ሰዎች ጋር ስብሰባ ተሰብስቦ ነበር፡፡ በስብሰባውም ወቅት ሌሎች ተሰብሳቢዎችን ሇማስዯመም ፈልጎ እንዱህ አሇ "እኔ ምዴር ምን ያህል ትልቅ እንዯሆነችና በትክክል ምን ያህል ስፋት እንዲላት አውቃሇሁ፡፡ ነገ ስንገናኝ እነግራችኋሇው፡፡ "በስብሰባውም ላይ ያለት ተሰብሳቢዎች በፍጹም አላመኑትም ነበርና እንዱያሲዝ ጠየቁት በመሸም ጊዜ ያሇውን ሀብት ሁለ ተወራርድ በቁጭት ወዯ ቤቱ ተመሇሰ፡፡ ባሇቤቱም የሆነ ችግር እንዲጋጠመው አስተዋሇች፡፡ "ዛሬ ምን አይነት ችግር አጋጥሞህ ነው ምግብ ሳትመገብ ወዯ መኝታ የሄዴከው?" ብላ ጠየቀችው፡፡ "የመሬት ስፋት ምን ያህል እንዯሆነ አውቃሇሁ ብዬ ያሇኝን ንብረት ሁለ አስያዝኩኝ ነገ እነግራችኋላው አልኳቸው፡፡" ሚስትየውም አንዴ ብልሃት መጥቶላት እንዱህ ብላ አፅናናችው "አታስብ ይሄ በጣም ቀላል ነገር ነው፡፡ ነገ የተባሇበት ቦታ ሂዴና
አንዴ ችካል ቸክል ሇተሰብሳቢዎችም እንዱህ በላቸው መሬት ከዚህ ችካል በዚህኛው አቅጣጫ በጣም ብዙ ሺህ እርምጃ እንዯገና በሌላኛውም አቅጣጫ በጣም ብዙ ሺህ እርምጃ ይርቃል፡፡ እነሱም ያልከውን ካላመኑህ፣ ሄዯው እንዱሇኩ ንገራቸው፡፡ ይህንን ማረጋገጥ ከቻለ እና አንተ የተናገርከው ትክክል አሇመሆኑ ከተረጋገጠ፣ ያስያዝከውን ንብረት ሁለ ይወስደ፡፡" ሰውየውም ምክሯን ሰምቶ በጣም ዯስ ብሎት እራቱን በልቶ ወዯ መኝታው አመራ፡፡
በሚቀጥሇውም ቀን ባሇቤቱ እንዯነገረችው አዯረገ በእርግጥም ማናቸውም ተሰብሳቢዎች በነገራቸው ነገር እርገጠኛ አልነበሩም፡፡ ዯግሞም ያላቸውን ማረጋገጥ አልቻለም በመሆኑም ያስያዘውን ንብረት ሁለ አዲነ፡፡
ስሇሆነውም ነገር የሀገሪቱ ንጉስ ሰማ ንጉሱም ሰውየው ወዯሱ እንዱመጣ አስዯርጎ ጥያቄ ጠየቀው፡፡ "ማነው ይህንን ምክር የሇገሰህ ?" "ባሇቤቴ" ብሎ በቅንነት መሇሰላቸው፡፡ ንጉሱም የበሇጠ ሇማወቅ ፈልጎ "ሚስትህ ብልህ ነች:: ቆንጆም ነች ?" ብሎ ጠየቀው፡፡ ሰውየውም በዴጋሚ በግልጽ "አዎ ባሇቤቴ ብልህ ፣ ቆንጆ ፣እንዱሁም ወጣት ናት::" ብሎ መሇሰሇት:: "ባሇቤትህ ብልህ ቆንጆና ወጣት ከሆነች እርስዋ የምትገባው ሇንጉስ ነው ፡፡ ነገ ይዘሃትና እና እኔ አገባታሇሁ::" አሇው:: በዛም ቀን ሞኙ ሰውዬ በጣም ተበሳጭቶ ወዯቤቱ ተመሇሰ፡፡ "ባሇቤቱም ምን ተፈጠረ ሇምንዴን ነው ያዘንከው?" ብላ ጠየቀችው፡፡ "ንጉስ ስላንቺ ብልህነት ጠየቀኝ፡፡ እኔም አንቺ ብልህ ቆንጆና ወጣት እንዯሆንሽ ነገርኩት::
እሱም አንቺን ማግባት ይፈልጋል፡፡" ሚስትየውም ጭንቅላቷን እየነቀነቀች "አንተ ሞኝ ሰው ፤ሇምን ሇንጉስ እንዱህ ብሇህ ትነግረዋሇህ? ነገ ወዯንጉሱ ሂዴና በንጉሱ ውሳኔ እንዯተዯሰትኩና ሇሱና ላማካሪዎቹ ምግም እንዲዘጋጀሁ ንገረው:: " ሰውየውም ንጉሱን ጋበዘው ንጉሱም ወዯ ሴትየዋ ቤት መጣ ሚስትየውም የመመገቢያ ጠረጴዛ አዘጋጅታ ጠበቀቻቸው፡፡
ጠረጴዛውም ላይ ጎርጓዲ የስጋ ሰሀኖች አዯረገች:: ሰሀኖቹንም በተልባ ሞላቻቸው እያንዲንደንም ሰሀኖች በጨርቅ ሸፈነቻቸው፡፡ ጨርቆቹም በሱፍ፣ በሀር፣ በወርቅ የተሇበጡ ፣ በሚያምር ቀሇም የተጠሇፉ ጥልፎች ላይነን እና ጥጥ ነበሩ፡፡ ንጉሱም ወዯ መመገቢያው ክፍል ገብቶ ተቀመጠ ከዚያም የአንደን ሰሃን ጨርቅ ገሇጸ በሰሃኑ ውስጡም ያገኘው ተልባ ብቻ ነበር፡፡ እንዯገና ሌላኛውን ሰሃን ሲከፍተው በእሱም ውስጥ ያገኘው ተልባ ብቻ ነበር፡፡ እንዯገና ሌላኛውንም ሰሃን ሲከፍት በዕርሱም ውስጥ እንዯገና ሌላኛውን ሰሃን ሲከፍተው ያገኘው ተልባ ብቻ ነበር፡፡ ከዛም በሱፍ፣ በሀር፣ በላይነንና በሌላ ጨርቆች የተሸፈኑትን ሰሀኖች ከፍቶ ሁለም በተልባ እንዯተሞለ ሲያይ በጣም ተናዯዯ፡፡አየህ፡፡ "ሚስትህ እኛን አሞኘችን በእኛም ላይ ተሳሇቀች ምን ይሁን ብላ ነው የምታዯርገው?" ብሎ ሰውየው ላይ ጮኸበት፡፡
ሴትየዋም ወዯ መመገቢያው ክፍል ገብታ "ንጉስ ሆይ የኛ የሴቶች መልካችን ጠረጴዛው ላይ እንዯተመሇከቱት ጨርቆች ነው:: ጠረጴዛው ላይ ሇስላሳ፣ሻካራ ፣ ዯማቅና ውዴ ጨርቆች ይገኛለ፡፡ የሴቶች ውበትና ተፈጥሮም እንዯዚህ ነው፡፡ነገር ግን ውስጣችን እንዯተልባው አንዴ ነው፡፡ ቆንጆም ሆንን ፉንጋ የእኛ የሴቶች ማንነታችን አንዴ ነው፡፡ "ንጉሱም በሴትየዋ ሇባልዋ ባላት ታማኝነት ተዯነቀ፡፡ ባልዋን ትታ ንጉስ አግብታ በክብር ከመኖር ይልቅ ሇባልዋ ታማኝ ሆና መኖርን መምረጥዋን ተረዲ፡፡ በሴትየዋ
ብልህነትና በሰጠችው ምሳሌ በመዯነቅ በጣም ብዙ ገንዘብ ሰጣቸውና እንዱህም አላት "እኔ ባልሽንና አንቺን በመጥፎ ሃሳቤ አስዯነገጥኳችሁ ነገር ግን አንቺ በዚህ ዴንቅ ምሳሌሽ ከሀጥያት አዲንሽኝ፡፡
ተረቴን መልሱ አፌን በዲቦ አብሱ።
ተረት ከኢትዮጲያ፣ እትም አኒና ማይሇ፣ ከካርል ማይንሆንሆፍ፣ የአፍሪካውያን ተረት፣ ጀና 1917፣ ©ሙታቦ ር ተረት ፋውንዳሽን